የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሂዷል

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን ያካሄደ ሲሆን፤ በጉባኤው የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል ።
የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ስለተሰሩ ሥራዎች፣ የመንገድ ማስፋፊያዎች የኮሪደር ልማቱን ተሞክሮ በመውሰድ በፍጥነት እና በጥራት እንዲጠናቀቁ እየተደረገ ሳላለው ክትትል፣ የመብራት መቆራረጥን በዘላቂነት ለመፍታት ምን ታስቧል? ፣ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት በተለይ የጤና ተቋማት ግንባታ ላይ የተለየ ትኩረት ቢሰጥ የሚሉ ጥያቄዎች ከተነሱት መካከል ይጠቀሳሉ።
እንደ ሀገር እየተዋወቀ ያለውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ በአዲስ አበባ በፍጥነት እና በትኩረት ተግባራዊ ቢደረግ የሚሉ እና ሌሎችም ጥያቄዎችም ከምክር ቤቱ አባላት ተነስተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ መስጠታቸውን ከኢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል


                   የኮሙንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
                  ሚያዚያ 22/2017

የኮሪደር ልማቱን በሁሉም የመዲናዋ አካባቢዎች ለማዳረስ በቅደም ተከተል እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

መዲናዋ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት በሁሉም አካባቢዎች ለማዳረስ በቅደም ተከተል እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡
ከንቲባዋ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
ለውጡን ተከትሎ ለህዝባችን ቃል ገብተን እና ራዕያችን አድርገን የተነሳነው አዲስ አበባን እንደስሟ ውብና ተወዳዳሪ ከተማ ለማድረግ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ የህዝቡ ጥያቄ መሰረታዊ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የኮሪደር ልማቱ በተከናወነባቸው አካባቢዎች በርካታ ጥቅሞች እንደተገኙና በዚህም የመዲናዋ ነዋሪዎች ደስተኛ መሆናቸውንም ከንቲባ አዳነች አመልክተዋል፡፡
አዲስ አበባም እንደስሟ ውብ፣ለነዋሪዎቿ የምትመችና በዓለም አቀፍ ደረጃም ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን የኮሪደር ልማቱ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል፡፡
በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ መንገዶች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የአረንጓዴ ቦታዎች፣ የአውቶብስና የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ፌርማታዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና ሌሎችንም ያካተተው የኮሪደር ልማት ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታን እያስገኘ እንደሚገኝም ከንቲባዋ አመላክተዋል፡፡
የኮሪደር ልማቱ ባልተዳረሰባቸው የመዲናችን አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችንም የዚህ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በቅደም ተከተል እየስራን ነው ብለዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ያረጁና በመፈራረስ ላይ የሚገኙ ቤቶችን አፍርሶ ለመገንባ ጊዜና ገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች፣ ህብረተሰቡ እንደተለመደው በትዕግስት እንዲጠብቅና ለስራውም ተሳታፊ እንዲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳስበዋል ሲል የአዲስ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
የኮሙንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሚያዚያ 22/2017

10ኛው የኦዲተሮች ልምድ ልውውጥ በድሬደዋ

10ኛው ሀገር አቀፍ የዋና ኦዲተሮች ውይይት በድሬደዋ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 10ኛው የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ በድሬደዋ ከተማ እየተካሄደ ነው።የድሬደዋ አስተዳደር ዋና ኦዲተር ፋኪያ መሐመድ በዚህ ወቅት÷የጋራ ምክክሩ ደረጃውን የጠበቀ የኦዲት ተግባራት በማከናወን የመንግስትና የህዝብ በጀት በአግባቡ ለታለመለት ተግባር እንዲውል የሚያስችሉ ግንዛቤዎችን ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል።
የልምድ ልውውጡ ደረጃውን የጠበቀ የክዋኔ ኦዲት ለመተግበር የሚያስችል ግንዛቤ የሚፈጥር መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡በተጨማሪም በየደረጃው በሚገኙ ተቋማት ውስጥ የተጠያቂነት ሥርዓትን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል መደላድል እንደሚፈጥር ነው የገለፁት፡፡በውይይቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ምክርቤት አፈጉባዔ ፈትሂያ አደን፣ የየክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ዋና ኦዲተሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ለሶስት ቀናት በሚዘልቀው ውይይት ላይ ለተሞክሮ የሚያግዙ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው የገኛል።

ኃላፊነትና ተጠያቂነት በማረጋገጥ የመንግስት ሀብትና ንብረትን ከብክነት እና ምዝበራ መከላከል

 “ኃላፊነትና ተጠያቂነት በማረጋገጥ የመንግስት ሀብትና ንብረትን ከብክነት እና ምዝበራ መከላከል” ቢሚል ርዕስ ከባለ ድርሻ አካላት (ኦዲት ተደራጊ ተቋማት) አመራሮች ጋር ውይይት ተደረገ።

መጋቢት 23/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከባለድርሻ አካላት (ኦዲት ተደራጊ ተቋማት) አመራሮች ጋር “ኃላፊነትና ተጠያቂነት በማረጋገጥ የመንግስት ሀብትና ንብረትን ከብክነት እና ምዝበራ መከላከል”  በሚል ርዕስ ላይ በጁፒተር ሆቴል ውይይት አደረገ። ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻሉ የውይይቱን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፤ በቀረበውም ሰነድ ላይ ተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በቀረበው ጥያቄ ላይ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ የተከበሩ አቶ ማሾ ኦላና እና ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻሉ  ምላሽ ሰጥተውበት ውይይቱ ተጠናቅቋል።

የ2016 ዓ.ም እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ግምገማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ግምገማ አደረገ።

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት የመ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት በዛሬው ቀን ማለትም በ20/12/2016 ዓ.ም በኢትጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትውት በዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ማሞ አማካኝነት ቀርቧል።

በመጨረሻም  በቀረበው ሰነድ ላይ የመ/ቤቱ ሰራተኞች አስተያየት እና ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎች እና  አስተያየቶች የመ/ቤቱ ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻሉ መልስ ሰጥተውበት ግምገማው ተጠናቅቋል።

የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ

ሀምሌ 09/2016 ዓ.ም የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ በሚል መሪ ቃል የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መረህግብር በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የችግኝ ተከላ መረሀ-ግብር ተካሄደ፤
በአረንጓዴ አሻራ መስክ የሚጠበቀው ውጤት እንዲመጣ ችግኝ መትከልና መንከባከብ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ ገለጹ
ያለምንም ልዩነት ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ – ግብር ስኬት በጋራ መቆም እንደሚገባ የልደታ ከ/ከተማ ክፍለ ከተማ ም/ ስራ አስፈፃሚ ክብርት ወይዘሮ ዮዲት ሰለሞን ገልጸዋል መ/ቤቱ በየዓመቱ የሚከናወነውን የችግኝ ተከላ ስራ የሚያከናውን ሲሆን ከመትከል ባሻገር ለችግኞች እንክብካቤ የሚደረግ መሆኑንና አምና ከተተከሉ ችግኞች መካከል 98 ፐርሰንቱ የጸደቀ ሲሆን የመ/ቤቱ ሰራተኞችና አመራሮችም በችግኝ ተከላው መረሀግብር ላይ መሳተፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ሪፖርት

መስሪያ ቤታችን የዘጠኝ(9) ወር አፈፃፀም ሪፖርት  ከአጠቃላይ የመ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር በእስቴይኢዚ(Stayeasy) ሆቴል  የገመገመ ሲሆን  የዘጥኝ ወር ሪፖርቱን ያቀረቡት የእቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ተወካይ  የሆኑት አቶ ደረጄ ማሞ ናቸው።  በቀረበው ሪፖርት ላይም ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻሉ  ከሰራተኞች ጋር ውይይት አድርገዋል።