**************************************በመማክርት ጉባኤ የምስረታ መድረክ የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ በመመስረት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የአዲት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተገቢው ሁኔታ ለመምራትና አስተማማኝ መረጃ እንዲያገኝ የመንግስት ተቋማት የተመደበላቸውን ሀብት ሕግና መመሪያን ተከትለው በአግባቡ እንዲጠቀሙ በዕቅድና ኢኮኖሚያዊ በሆነ መንገድ በመምራት የሚጠበቅባቸው በመሆኑ በእቅድ የያዟቸውን ተግባራት ከግብ እንዲያሳኩና ህገወጥ የመንግስት ሀብትና ንብረት አጠቃቀምን በተመለከተ በኦዲት ተጣርቶ እንዲቀርብላቸው ከፍትህ አካላት የሚቀርቡ የኦዲት ይደረግልኝ ጥያቄዎችን በመቀበል ለውሳኔ የሚያግዝ የኦዲት ሥራ ውጤት በማቅረብ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል ገልፀዋል፡፡
ሆኖም የአጋዥ አካላት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማትን እንዲሁም የተገልጋዮችን ተሳትፎ በማጎልበት በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት ግልጽነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ይህ የመማክርት ጉባኤ መመስረቱን ገልፀው መማክርት ጉባኤው በከተማ አስተዳደሩ ያሉ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ተገልጋይ ህብረተሰቡ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ግልጽ የሆነ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፤ በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተገልጋዩ ህብረተሰብ በአግባቡ እንዲረዳው ማስቻልን መሰረት ያደረገ አላማ ይኖረዋል ብለዋል።
የመማክርት ጉባኤው ከተገልጋይ ከሲቪክ ማህበራት ከባለድርሻ አካላትና የተቋሙ/ጽ/ቤት በሚወከሉ አካላት የሚመሰረት የመማክርት ጉባኤ ሲሆን ጉባኤው የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የመማክርት ጉባኤ ስራ አፈፃሚ ሰብሳቢና አባላትና በመምረጥ የመመስረቻ ጉባኤው ተጠናቋል ።
********************************
የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም


