የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር
አዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለሠራተኞቹ በሥነ ምግባርና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ፡፡
በሥልጠናው የሠራተኞችን የሥነ ምግባር ግንዛቤ ለማሳደግ፣ በሥራ እፈጸጸም ወቅት የሙያ ሥነ ምግባር መርሆዎችን በተግባር እንዲያውሉ ለማስቻልና በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች የተገልጋዩን ያገልግሎት ፍላጎት ከማርካት ባሻገር የአስራር ግልፀኝነትና ተጠያቂነት አስራር ስርዓትን በሁለም ሙያተኞች ማስረፅን ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ መስሪያ ቤቱ በሥነ ምግባርና በመልካም አስተዳደርዙሪያ የሚሰጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ገልፅው! ሠራተኞች የሙያ ሥነ ምግባርን በዕለት ተዕለት ተግባራቸው እንዲያንጸባርቁና የተቋሙን ተልዕኮ በብቃት በመፈፀም ረገድ ሁለም ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን ባግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዋና ኦዲተር አክለው ዋና ኦዲተር መስሪያቤቱ ግልፅ የሆነ የአሰራር ስርአት ያለው መሆኑን ጠቅሰው የስነ-ምግባር መርሆዎችን መሰረት ያደረገ የሙያ ስነ-ምግባርን አገልግሎት በምንሰጥባቸው ተቋማት በመተግበር ለተቀመጡት የሙያና የስነ-ምግባር መርሆዎች መገዛት ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ የስነምግባርና የፀረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሲሳይ በፍቃዱ ስነምግባር በምክንያታዊነት የተደገፈ መልካም ውሳኔ መወሰን ወይም መምረጥ መሆኑን ጠቅሰው ስነምግባር ቅቡልነት የሌላቸውን ባህርያት እና ድርጊቶችን የምንቆጣጠርበት ሰብዓዊ ልጓም ነው ብለዋል፡፡
አቶ ሲሳይ አክለው ስነ-ምግባር! መልካም ስምን፣ ማንነትን፡ አመኔታን እና ቅቡልነትን ለመገንባት አውንታዊ ግንኙነትን ለመመስረት እንዲሁም የሕወትና የስራ መርህን በአግባቡ ለመምራት ያለውን ጉልህ ሚና አስታውሰው የምንሰጠውን አገልግሎት ከስነ-ምግባር ጋር በማስተሳሰር ባለሙያዎች የስነ-ምግባር መርሆዎችን ሊጠቀሙባቸውና ሊያከበራቸው የሚገባ የጋራ እሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡
በመድረኩ የሥነ ምግባር መርሆዎችን በሥራ ላይ የመተግበር አስፈላጊነት፡ የሠራተኞች የሙያ ኃላፊነት፣ ሕግና ደንብን የማክበር ግዴታ እንዲሁም ከሙስናና ከመነ ምግባር ጉድለት ጋር ተያይዘው ሊክስቱ የሚችሉ ችግሮችን በመከላከል ረገድ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እና ተቋሙ የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚያድርግው ጥረት የሰራተኞችን ሚና በግልጽ ተመላክቷል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.