Skip to content
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
-
የፋይናንሻልና ህጋዊነት ኦዲት
-
የፐርፎርማንስ(የክዋኔ ኦዲት)
-
የገቢ ኦዲት
-
የአከባቢ ኦዲት
-
የልዩ ኦዲት(የማጭበርበር ኦዲት)
-
የስልጠና አገልግሎት
-
የኦዲት ግኝትና ጥንቅር ግብረ-መልስ አገልግሎት
የመስሪያ ቤቱ ስልጣንና ተግባር
-
በከተማው አስተዳደር የመንግስት መ/ቤቶችና የመንግስት ልማት ድረጅቶች ላይ የፋይናንስና ህጋዊነት ኦዲት፣ የክዋኔ ኦዲት፣ የገቢ ኦዲት፣የአከባቢ ኦዲት፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ ኦዲት ፣ ልዩ ኦዲትና እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች ኦዲቶችን ያደርጋል ያስደርጋል።
-
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከህዝብ አገልግሎት ሰጪና ከመንግስት ተቋማት ጋር ካለው ኮንትራት ውል አፈፃፀም ጋር የሚገናኙ ጉዳዮችን በተመለከተ የግል ድርጅቶችን አስፈላጊ መረጃዎችንና ሪፖርቶችን ሊመረምር ይችላል።
-
በመንግስት መ/ቤቶች ወይም ድርጅቶች ኦዲት ግኝቶች ላይ ክትትል ያደርጋል፤ ስለአፈፃፀማቸውም ገምግሞ ግብረ-መልስ ይሰጣል። ስለሁኔታው ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል።
-
ለመንግስት መ/ቤቶችና ድርጅቶች የተሰጠ እርዳታ እና ብድር ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል።
-
ውጤታማ የሀብት አጠቃቀምን ለማሳደግና ወቅታዊ ለውሳኔ አጋዥ የሆነ የኦዲት ሪፖርት ለማቅረብ እንዲረዳው ሂሳብ ከመዘጋቱ በፊት የኦዲት ስራውን ሊጀምር ይችላል።
-
ከፌደራልና ከክልል ዋና ኦዲተር መስሪያቤቶች ከግል ኦዲት ድርጅትና ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች ጋር በመመካከር የኦዲት ስርዓትና ደረጃ በሚዳብርበት ሁኔታ የስራ ግንኙነትና ትብብር ያደርጋል።
-
በከተማ አስተዳደር ውስጥ የኦዲት ሙያ ትክክለኛውን ፈር ይዞ እንዲዳብር ጥረት ያደርጋል። አስፈላጊውን ቁጥጥር ያደርጋል።
-
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የአስተዳደሩ መ/ቤት የውስጥ ኦዲተሮች የመ/ቤታቸውን ሂሳብና ንብረት ኦዲት አድርገው ውጤቶን እንዲገልፁለት ሊያደርግ ይችላል።
-
የከተማ አስተዳደሩ የፋይናንስ ቢሮ ስለ ገንዘብ አጠባበቅ፣ የሂሳብ አያያዝና የንብረት አስተዳደር በተመለከተ በሚዘጋጀው መመሪያ ላይ አሰፈላጊውን ምክርና ሀሳብ ይሰጣል።
-
ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች እና ልማት ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለውስጥ ኦዲተሮች ስልጠና ይሰጣል፤ የውስጥ ኦዲት አሰራርን በማጥናት ለአስተዳደሩ አካላት ተገቢውን ምክር ይሰጣል፤ ያሰጣል።
-
አንድ ሂሳብ የወንጀል ጥርጣሬ ባለበት ሁኔታና ታማኝነት በጎደለው አኳኋን መያዙን ለማመን በቂ ምክንያት ያለው እንደሆነ ሂሳቡን የሚመለከቱ ጽሑፎች፣ መዘክሮች፣ መዝገቦች፣ ሠነዶችና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው መረጃዎችን ያሽጋል፤
-
በከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች ህግ ውስጥ የተመለከቱት መሰረታዊ ዓላማዎችና የሰራተኛው መብትና ጥቅም እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማው ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት ለመሥሪያ ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞችን በራሱ ያስተዳድራል፣ ያሰናብታል፤ ይቀጥራል፣
-
የሠራተኞቹን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅሞች አጥንቶ ለምክር ቤት ያቀርባል ፣ ሲወሰን ተግባራዊ ያደርጋል፤
-
መስሪያ ቤቱ በጀት አዘጋጅቶ ለምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲፀድቅ፤ ስራ ላይ ያውላል።