Archives September 2026

መሰረታዊ የሥነ-ምግባር መርሆዎችን እና እሴቶችን ሁሉም ሙያተኛ ሊያከብራቸውና ሊከተላቸው እንደሚገባ ተገለፀ።


የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለኦዲተሮችና አስተዳደር ሰራተኞች የሙያ ስነምግባር መርሆዎች፣ ምንነት እንዲሁም የሙያ ስነምግባር ያለው ሚናና ጠቀሜታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናውን ለሰራተኞች የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የፋይናንስና ህጋዊነት ም/ዋና ኦዲተር ወ/ሮ አንድነት ብዙሰው የሙያ ስነምግባር ምንነት፣ ሙያተኞች ሊከተሏቸው የሚገቡ መርሆዎች፣ የስነምግባር ግዴታና ሚና በተለይም በኦዲት ስራ የሚጠበቁ የሙያ ብቃት ስነምግባርና ተጠያቂነት አሰራር ስርአት ዝርዝር ጉዳዮችን አብራርተዋል።

ወ/ሮ አንድነት በማብራሪያቸው በስነምግባር ነፃነት፣ ታማኝነት፣ ገለልተኝነት፣ ሚስጥር ጠባቂነት፣ ሙያዊ ብቃትና የተጠያቂነት አሰራር እንደ ዋና የስነምግባር መርሆዎች በማንሳት፤ እነዚህ መርሆዎች የኦዲት ስራ ጥራትን ለማሻሻልና የህዝብ እምነትን ለማስጠበቅ ያላቸውን ጉልህ ሚናና አስፈላጊነት ገልፀዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሰራተኞች በየዕለት ተግባራቸው የሙያ ስነምግባርን በመጠበቅ ለተቋሙ ውጤታማነት፣ ለግልፅነትና ለተጠያቂነት ያላቸውን ድርሻ እንደሚያጠናክሩ ገልፀው በስልጠናው የቀረቡ ሀሳቦች በስራ ቦታ የሚያጋጥሙ የስነምግባር ተግዳሮቶችን በተገቢ መንገድ ለመፍታት፣ የሙያ ስነምግባርን ለማሳደግና የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል ረገድ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ በቀጣይም የሰራተኞችን ሙያዊ አቅም፣ ስነምግባርና የስራ ብቃት ለማሳደግ የተለያዩ የስልጠናና የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ወ/ሮ አንድነት ብዙሰው የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የፋይናንስና ህጋዊነት ም/ዋና ኦዲተር ሰራተኞች በተቋማቸው ሊከተሉ የሚገባቸውን የሙያ ስነምግባር በማጠቃለያቸው መሠረታዊ የሥነ-ምግባር መርሆዎችና ግዴታዎች፤ ታማኝነት፣ ሐቀኝነት፣ ቅንነት፣ ሙያዊ ጥንቃቄ፣ ሚስጥራዊነት፣ ግልፅነት፣ ነጻነት፣ ገለልተኝነትና ፍትሐዊነት፣ የጥቅም ግጭትን መክላክል፣ ሙያዊ ብቃት እና ሙያዊ ትጋት ሁሉም ሙያተኛ ሊከተላቸውና ሊያከብራቸው የሚገቡ መርሆዎች ናቸው ብለዋል።


የኮሙንኬሽን ዳይሬክቶሬት
ነሐሴ 26/2018