የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና የተጠሪ ተቋማትን የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ገመገመ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና የተጠሪ ተቋማትን የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ገመገመ።
ጥር 04/04/2018 አዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ፣ ለምክር ቤቱ ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት ጋር የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።
በመድረኩ ላይ ሁሉም ተጠሪ ተቋማት የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸማቸውን ያቀረቡ ሲሆን በተለይም እንደ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሪፎርም ያደረጉ ተቋማት ሪፎርሙ ያመጣው ለውጥና ተግዳሮቶችን ላይ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በመልካም አስተዳደር ፤ሙስናን ከመከላከል አኳያ እና ከሌብነትና ከብልሹ አሠራር አንፃር በከተማዋ ለታየው የልማት ስራ ስኬት ተቋማቱ ስላበረከቱት ድርሻ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ የተከበሩ ዶ/ር ማሾ ኦላና፤ ተጠሪ ተቋማቱ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ የታቀዱ ስራዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ከዚያም በላይ የሆኑ ተግባራትን በፍጥነትና በጥራት ማከናወናቸው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ተቋማቱ እርስ በእርስና ከሌሎች አካላት ጋር በቅንጅት በመስራታቸው ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን ተናግረዋል፤ በተጨማሪም የላቀ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማረጋገጥ ረገድ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ጭምር ገልፀዋል።
የመንግስት ዋና ተጠረው፤ በተጨማሪም የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ማጠናከር፣ የህጎችን ተፈጻሚነት በኦዲት መፈተሽ እና የህዝብና የመንግስት ሀብት በግልጽነትና በተጠያቂነት መመራቱን ማረጋገጥ እንደሚገባ አቅጣጫ አሰቀምጠዋል።
የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ማሾ ኦላና አክለውም፣ በባለፈው በጀት ዓመት የታዩ መልካም አፈጻጸሞችን በማስቀጠልና ውስንነቶችን በመለየት ተቋማዊ ጥንካሬን መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው፣ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ቀሪ የትኩረት ስራዎችን እንደሚያከናውኑ ገልጸዋል። የከተማውን ነዋሪ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በህግ የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በመጠቀም በትጋት ለመስራት ቃል ገብተዋል.። የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት














































