Archives January 2024

ዘጠነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚያደርገው የኦዲት ስራዎች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምድ ልውውጥ መርሀ -ግብር ሶስተኛው ቀን ውሎ:-

በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር /ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የልምድ ልውውጥ እና የጋራ የምክክር ጉባኤ ዛሬ ሶስተኛው ቀን ላይ ነው፡፡ በዛሬው ፕሮግራም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር /ቤት እና ሲዳማ ክልል ዋና ኦዲተር /ቤት ተሞክሮአቸውን አቅርበዋል በከሰዓት ፕሮግራም በቀረቡት ሁለቱም ሰነዶች ላይ ውይይት ይደረጋል

ዘጠነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚያደርገው የኦዲት ስራዎች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምድ ልውውጥ መርሀ -ግብር በሁለተኛው ቀን ውሎ:

በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መ/ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የልምድ ልውውጥ እና የጋራ የምክክር ጉባኤ ዛሬ ሁለተኛውን ቀን ላይ ነው፡፡ በዛሬው ፕሮግራም የአማራ ዋና ኦዲተር መ/ቤት እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ተሞክሮአቸውን አቅርበዋል በከሰዓት ፕሮግራም በቀረቡት ሁለቱም ሰነዶች ላይ ውይይት ይደረጋል ።

ዘጠነኛው የአዲስ አበባ ከተማ  ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚያደርገው የአዲት ስራዎች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምድ ልውውጥ መርሀ -ግብር መካሄድ ጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከአጎራባች ክልሎች ጋር እያካሄደ ባለው የተሞክሮና የልምድ ልውውጥ መረሀ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ፤የአማራ ክልል ፤የሲዳማ ክልል ፤የደቡብ ምዕራብ ክልል፤የደቡብ ኢትይጵያ ክልል፤የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፤የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤የሃራሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና እና ምክትል ኦዲተሮች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምዳቸውን በተዘጋጀው የቼክ ልስት መሰረት ለውይይት መነሻ ይሆን ዘንድ እያቀረቡ ይገኛሉ ።


የአዲስ አበባ ከተማ  ምክር ቤት ምክትል  አፈ ጉባኤ ወ/ት ፈይዛ መሐመድ ፤የመንግሥት በጀት ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጋትዌች ዎርን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻል ተገኝተው የኦዲት ስራዎች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምዶችን እያዳመጡ ነው።


መንግሥት ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሥራዎችን በሚፈለገው አግባብ ማስተዳደርና መምራት እንዲችል ህግና የአሰራር መመሪያን የተከተለ ጠንካራ የፋይናንስ የቁጥጥር ስርዓት መኖር አስፈላጊ መሆኑን በመረሀ-ግብሩ መክፈቻ ላይ የጠቆሙት የአዲስ አበበ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ት ፈይዛ  መሐመድ ኦዲት የመንግሥት ሀብትና ንብረትን ከብክነት ፣ከስርቆትና ሙስና ለመከላከል አይነተኛ መሣሪያ መሆኑን ተረድተን ሁሉችንም በተገኘንበት በዚሁ አግባብ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል ።


የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤቶች የየዕለት የፋይናንስ ቁጥጥር ስራችሁን ከዓለም አቀፍ የኦዲት አተገባበር ተጨባጭ እንቅስቃሴዎች ጋር በማጣጣምና የዘርፉን ባለሙያዎች የሙያ ነጻነት በማክበር የመንግስት ሀብት ተጠብቆ እንዲጨምር ከማድረግ ረገድ ተወዳዳሪና ጠንካራ ሆናችሁ በመውጣት ኃላፊነታችሁን በአግባቡ ልትወጡ ይገባልም ሲሉ ምክትል አፈ -ጉባኤዋ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ።


ከአጎራባች ክልሎች ጋር እየተደረገ ያለው የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የተሞክሮና የልምድ ልውውጥ መድረክ የአፈጻጸም ሪፖርቶችን መነሻ ባደረገ መልኩ ክፍተቶችን ለይቶ መሙላትን ታሳቢ ባደረገ ውይይት እስከ መጪው አርብ ድረስ በልዩ ትኩረት የሚከናወን መሆኑን ከመረሀ-ግብሩ ለመረዳት ተችሏል ።4014:28