Archives 2024

የ2016 ዓ.ም እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ግምገማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ግምገማ አደረገ።

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት የመ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት በዛሬው ቀን ማለትም በ20/12/2016 ዓ.ም በኢትጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትውት በዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ማሞ አማካኝነት ቀርቧል።

በመጨረሻም  በቀረበው ሰነድ ላይ የመ/ቤቱ ሰራተኞች አስተያየት እና ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎች እና  አስተያየቶች የመ/ቤቱ ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻሉ መልስ ሰጥተውበት ግምገማው ተጠናቅቋል።

የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ

ሀምሌ 09/2016 ዓ.ም የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ በሚል መሪ ቃል የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መረህግብር በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የችግኝ ተከላ መረሀ-ግብር ተካሄደ፤
በአረንጓዴ አሻራ መስክ የሚጠበቀው ውጤት እንዲመጣ ችግኝ መትከልና መንከባከብ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ ገለጹ
ያለምንም ልዩነት ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ – ግብር ስኬት በጋራ መቆም እንደሚገባ የልደታ ከ/ከተማ ክፍለ ከተማ ም/ ስራ አስፈፃሚ ክብርት ወይዘሮ ዮዲት ሰለሞን ገልጸዋል መ/ቤቱ በየዓመቱ የሚከናወነውን የችግኝ ተከላ ስራ የሚያከናውን ሲሆን ከመትከል ባሻገር ለችግኞች እንክብካቤ የሚደረግ መሆኑንና አምና ከተተከሉ ችግኞች መካከል 98 ፐርሰንቱ የጸደቀ ሲሆን የመ/ቤቱ ሰራተኞችና አመራሮችም በችግኝ ተከላው መረሀግብር ላይ መሳተፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ሪፖርት

መስሪያ ቤታችን የዘጠኝ(9) ወር አፈፃፀም ሪፖርት  ከአጠቃላይ የመ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር በእስቴይኢዚ(Stayeasy) ሆቴል  የገመገመ ሲሆን  የዘጥኝ ወር ሪፖርቱን ያቀረቡት የእቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ተወካይ  የሆኑት አቶ ደረጄ ማሞ ናቸው።  በቀረበው ሪፖርት ላይም ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻሉ  ከሰራተኞች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ዘጠነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚያደርገው የኦዲት ስራዎች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምድ ልውውጥ መርሀ -ግብር ሶስተኛው ቀን ውሎ:-

በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር /ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የልምድ ልውውጥ እና የጋራ የምክክር ጉባኤ ዛሬ ሶስተኛው ቀን ላይ ነው፡፡ በዛሬው ፕሮግራም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር /ቤት እና ሲዳማ ክልል ዋና ኦዲተር /ቤት ተሞክሮአቸውን አቅርበዋል በከሰዓት ፕሮግራም በቀረቡት ሁለቱም ሰነዶች ላይ ውይይት ይደረጋል

ዘጠነኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚያደርገው የኦዲት ስራዎች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምድ ልውውጥ መርሀ -ግብር በሁለተኛው ቀን ውሎ:

በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መ/ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የልምድ ልውውጥ እና የጋራ የምክክር ጉባኤ ዛሬ ሁለተኛውን ቀን ላይ ነው፡፡ በዛሬው ፕሮግራም የአማራ ዋና ኦዲተር መ/ቤት እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ተሞክሮአቸውን አቅርበዋል በከሰዓት ፕሮግራም በቀረቡት ሁለቱም ሰነዶች ላይ ውይይት ይደረጋል ።

ዘጠነኛው የአዲስ አበባ ከተማ  ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከአጎራባች ክልሎች ጋር የሚያደርገው የአዲት ስራዎች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምድ ልውውጥ መርሀ -ግብር መካሄድ ጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከአጎራባች ክልሎች ጋር እያካሄደ ባለው የተሞክሮና የልምድ ልውውጥ መረሀ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ፤የአማራ ክልል ፤የሲዳማ ክልል ፤የደቡብ ምዕራብ ክልል፤የደቡብ ኢትይጵያ ክልል፤የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፤የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤የሃራሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና እና ምክትል ኦዲተሮች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምዳቸውን በተዘጋጀው የቼክ ልስት መሰረት ለውይይት መነሻ ይሆን ዘንድ እያቀረቡ ይገኛሉ ።


የአዲስ አበባ ከተማ  ምክር ቤት ምክትል  አፈ ጉባኤ ወ/ት ፈይዛ መሐመድ ፤የመንግሥት በጀት ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጋትዌች ዎርን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻል ተገኝተው የኦዲት ስራዎች የአፈጻጸም ተሞክሮና ልምዶችን እያዳመጡ ነው።


መንግሥት ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሥራዎችን በሚፈለገው አግባብ ማስተዳደርና መምራት እንዲችል ህግና የአሰራር መመሪያን የተከተለ ጠንካራ የፋይናንስ የቁጥጥር ስርዓት መኖር አስፈላጊ መሆኑን በመረሀ-ግብሩ መክፈቻ ላይ የጠቆሙት የአዲስ አበበ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ት ፈይዛ  መሐመድ ኦዲት የመንግሥት ሀብትና ንብረትን ከብክነት ፣ከስርቆትና ሙስና ለመከላከል አይነተኛ መሣሪያ መሆኑን ተረድተን ሁሉችንም በተገኘንበት በዚሁ አግባብ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል ።


የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤቶች የየዕለት የፋይናንስ ቁጥጥር ስራችሁን ከዓለም አቀፍ የኦዲት አተገባበር ተጨባጭ እንቅስቃሴዎች ጋር በማጣጣምና የዘርፉን ባለሙያዎች የሙያ ነጻነት በማክበር የመንግስት ሀብት ተጠብቆ እንዲጨምር ከማድረግ ረገድ ተወዳዳሪና ጠንካራ ሆናችሁ በመውጣት ኃላፊነታችሁን በአግባቡ ልትወጡ ይገባልም ሲሉ ምክትል አፈ -ጉባኤዋ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ።


ከአጎራባች ክልሎች ጋር እየተደረገ ያለው የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የተሞክሮና የልምድ ልውውጥ መድረክ የአፈጻጸም ሪፖርቶችን መነሻ ባደረገ መልኩ ክፍተቶችን ለይቶ መሙላትን ታሳቢ ባደረገ ውይይት እስከ መጪው አርብ ድረስ በልዩ ትኩረት የሚከናወን መሆኑን ከመረሀ-ግብሩ ለመረዳት ተችሏል ።4014:28