አለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ!

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የዲጂታል ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ለማስጀመር የሙከራ ስልጠና ሰጠ፡፡

የሙከራ ማስጀመሪያ ስልጠና የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌትነት ባንቴ እንዳሉት የዲጂታል ቅሬታ ማቅረቢያ ኢ ሰርቪስ የተቋማት የውስጥና የውጭ ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ በየትኛውም ጊዜ ቅሬታቸውን ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው የበለፀገው ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለተቋማት አገልግሎታቸውን ለማዘመንና የተገልጋዮቻቸውን የአገልግሎት እርካታ ለማሰደግ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ በበኩላቸው የሚሰጡ አገልግሎቶች የህብረተሰቡንና የባለድርሻ ተቋማትን የአገልግሎት እርካታ ለመፍጠርና ለማሳደግ የሚሰራ መሆኑን ገልፀው በአገልግሎት ሂደት የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን ለማቅረብና ለመፍታት ከወረቀት ንክኪ ነፃ የዲጂታል ቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓት መፈጠሩ ተገልጋዩ ባለበት ሁኔታና ቦታ ለሚያቀርበው ቅሬታ እልባት ለመስጠት ትልቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ዋና ኦዲተሩ አክው የውስጥ ቅሬታዎች በአቻ ፎረምና በስትራቴጂክ ካውንስል ቅሬታዎች ቀርበው የሚፈቱ መሆኑን ገልፀው እነዚህ አማራጮችን ለማያገኙ ተገልጋዮች ይህ የዲጂታል ቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓት ተገልጋዩንና ተቋማትን የበለጠ የሚያቀራርብና ለችግሮች እልባት ለመስጠት ተጠቃሽ ሚና አለው ብለዋል፡፡

******************************

የኮምንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ህዳር 12/2017 ዓ.ም