Archives November 2025

“ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት”

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን የመስሪያ ቤቱ አመራርና ሰራተኞች በተለያዩ ሁነቶች አከበሩ፡፡

********************************

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አምንቴ መቻሉ በመርሀ-ግብ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሚያዝያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም ባካሔደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የኤፌዴሪ ህገ መንግስት የፀደቀበትን ህዳር 29 ቀን የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተብሎ በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ሲወስን የውሳኔው ዓላማ የኢትዮጵያ ህዝቦች መክረውና ፈቅደው ያጸደቁት ህገ-መንግስት ያስገኘላቸውን ጥቅሞች እንዲያስቧቸው መብቶችና ነጻነቶቻቸውን ጠብቀው ማቆየት ብቻ ሳይሆን እርስ በእርስ የሚተዋወቁበት ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውንና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት፤አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩበት፤ የጋራ እምነቶቻቸውንና ተስፋቸውን የሚጋሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡

ዋና ኦዲተር አምንቴ መቻሉ አክለው የብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በ1999 ዓ.ም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት ”ሕገ-መንግስታዊ ቃል ኪዳን የአብሮነታችን መገለጫ ነው” በሚል መሪቃል በአዲስ አበባ ከተማ የተከበረ ሲሆን ይህም ላለፉት 19 ዓመታት በተከታታይ በተለያዩ ኩነቶች ሲከበር መቆየቱን ገልፀው 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለሕብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ሂዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሚከበር መሆኑን ጠቅሰው የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትም ከዚህ በመነሳት ይህን ህገ-መንግስታዊ ዋስትና የተረጋገጠበት የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል ብለዋል፡፡

ለተሳታፊዎች የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የኮልፌ ክ/ከተማ የብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ት/ቤት የማስፈፀም የአቅም ግንባታ ስራዎች አስተባሪ አቶ ፍቃዱ ቀቀባ አስተባባሪ እንዳሉት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት መከበር ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና ያረጋገጠው የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት የጸደቀበትን ቀን ህዳር 29 በየዓመቱ በተለያዩ ሁነቶች ላለፉት 19 ዓመታት ሲከበር መቆየቱን አስታውሰው በዚህ አመት “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ለ20ኛ ግዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ሲከበር በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ፌዴራላዊ ሥርዐት ማእቀፍ የተገነባ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር ማደረግን አላማ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

********************************

ህዳር 19/2018 ዓ.ም

የኮምንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

አለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ!

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት «ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!» በሚል መሪ ቃል በዓለም ለ22ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ21 ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ ባስተላለፉት መልክት ተቋማችን ከሁሉም በላይ በሙስና ጉዳይ ተልእኮ ወስደን በተደራጀና ተቋማዊ አሰራር በሆነ ሁኔታ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን መከላከል እንደ ሀገር ደግሞ አዋጆች ደንቦች ወጥተዋል ይህን መሰረት አድርገን እንደ አንድ የኦዲት ባለሙያ ሙስናን መከላከል ብቻ ሳይሆን በሙስናና ብልሹ አሰራር የባከነን የመንግስትና የህዝብ ሀብት ማስመለስ ይገባል ብለዋል።

ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ አክለው በመስሪያ ቤቱ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመታገል አደረጃጀትና አንድ የስራ ክፍል ፈጥሮ በተግባር በፀረ ሙስናና ብልሹ ከሰራር ትግል ውስጥ መሆኑን በመግለፅ ሁሉም ሰራተኞች ለዛሬ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ከሙስናንና ብልሹ አሰራር የፃዳች ሀገር ለማስረከብ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ረቂቅ ምርምር እና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ ሙስና ማለት በግል ወይም በቡድን፣ በፖለቲካ መሪዎች ወይም በቢሮክራቶች ስልጣንና ሀላፊነትን መከታ በማድረግ የህዝብን ጥቅምና ፍላጎት ለግል ጥቅም የማዋል ኢ-ስነምግባርዊ ድርጊት ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ይህንና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ አለም አቀፍና አህጉራዊ የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽኖችን የተቀበለችና በርካታ እርምጃዎች እየወሰደች ትገኛለች እንደምትገኝ ጠቅሰው የስልጠናው ተሳታፊዎች የሙስና ወንጀልን ከመፈጸም በመቆጠብ ሌሎች እንዳይፈጽሙ ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ህዳር 18/2018 ዓ.ም

የኮምንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የዲጂታል ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ለማስጀመር የሙከራ ስልጠና ሰጠ፡፡

የሙከራ ማስጀመሪያ ስልጠና የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌትነት ባንቴ እንዳሉት የዲጂታል ቅሬታ ማቅረቢያ ኢ ሰርቪስ የተቋማት የውስጥና የውጭ ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ በየትኛውም ጊዜ ቅሬታቸውን ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው የበለፀገው ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለተቋማት አገልግሎታቸውን ለማዘመንና የተገልጋዮቻቸውን የአገልግሎት እርካታ ለማሰደግ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ በበኩላቸው የሚሰጡ አገልግሎቶች የህብረተሰቡንና የባለድርሻ ተቋማትን የአገልግሎት እርካታ ለመፍጠርና ለማሳደግ የሚሰራ መሆኑን ገልፀው በአገልግሎት ሂደት የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን ለማቅረብና ለመፍታት ከወረቀት ንክኪ ነፃ የዲጂታል ቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓት መፈጠሩ ተገልጋዩ ባለበት ሁኔታና ቦታ ለሚያቀርበው ቅሬታ እልባት ለመስጠት ትልቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ዋና ኦዲተሩ አክው የውስጥ ቅሬታዎች በአቻ ፎረምና በስትራቴጂክ ካውንስል ቅሬታዎች ቀርበው የሚፈቱ መሆኑን ገልፀው እነዚህ አማራጮችን ለማያገኙ ተገልጋዮች ይህ የዲጂታል ቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓት ተገልጋዩንና ተቋማትን የበለጠ የሚያቀራርብና ለችግሮች እልባት ለመስጠት ተጠቃሽ ሚና አለው ብለዋል፡፡

******************************

የኮምንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ህዳር 12/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በልዩ ኦዲት ዙሪያ ሲሰጥ የነበረውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አጠናቀቀ፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለአምስት ተከታታይ ቀናት በልዩ ኦዲት ላይ ያጠነጠነ ስልጠና ለልዩ ኦዲት ባለሙያዎቹ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ እንዳሉ በልዩ ኦዲት ስራዎቻችን የተቀመጡትን አለማቀፍ ስታንደርዶች በመጠበቅ ባለበጀት መ/ቤቶች የተበጀተላቸውን የህዝብ ሃብት በአግባቡ መጠቀማቸውን ለማረጋገጥና በማወቅም ሆነ በለማወቅ ለሚሰሯቸው ስህተቶች መፍትሄ እዲያበጁ ማስቻል እንዲሁም የሀገርና የህዝብን ሀብት ከብክነት ለመጠበቅና አንደ አንድ የመንግስት ኦዲት አድራጊ ተቋም ሁሉም የኦዲት ባለሙያ ሚናውን እንዲወጣ ለማስቻል ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

ዋና ኦዲተ አመንቴ መቻሉ አክለው የኦዲት ግኝትና ሂሳብ ጉለት ሲገኝ ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የተጠያቂነት አሰራር ስርዓትን ለማስፈን አስፈላጊውን የህግ ሂደት በመከተል ግልፀኝነትና የተጠያቂነት አሰራር ስረዓት እንዲሰፍን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በስልጠናው ማብቂያ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው በቀጣይ ስራቸው ላይ የተሻለ አቅም የሚሰጡ ጠቃሚ እውቀትና ክህሎቶችን ያስጨበጣቸው መሆኑን ጠቅሰው በተለይ በልዩ ኦዲት ስራ ላይ ሊሚያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችና ስጋቶችን በግልፅ ያመላከተ በመሆኑ የልዩ ኦዲት ስራዎቻችንን ውጤታማ ለማድረግ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡


የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም

የተቋማት ውስጥ ኦዲተሮች ተቋማት የሚበጀትላቸውን ሀብት ከብክነትና ብልሹ አሰራር ለመታደግ ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡

ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ!

********************************

መንግስት ለህብረተሰቡ ይጠቅማሉ የበጃሉ ያላቸውን ዘላቂ የልማት ስራዋችና አገልግሎቶች በተግባር መሬት ላይ አውርዶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማስቻል የመንግስት በጀትን ለሚጠይቁ ስራዎች ካለው ውስን ሀብት ቆንጥሮ ለነዚህ አገልግሎቶችና ዘላቂ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና ለተለያዩ ዎጪዎች በጀት ይመድባል፡፡

ታዲያ ይህ ውስን የመንግስትና የህዝብ ሀብት ለታለመለት አላማ ለማዋልና ሁሉም ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች በጀታውን በእቅድ ለያዟቸው ተግባራት በአግባቡ አውለው የመንግስትንና የህዝብን ሀብት ከብክነት፣ ምዝበራና ብልሹ አሰራር ለመከላከል ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ይሰራሉ፡፡

ይሁን እንጅ በተለያዩ ምክንያቶች ከመንግስት ለተቋማት የሚበጀተው ውስን ሀብት በብልሹ አሰራር ምንያት ለብክነትና ምዝበራ ሲጋለጥ ይስተዋላል እንደ ግሎባል ፋይናንሻል ክራይም ዘገባ በ2023 በአለም ላይ 485 ቢሊየን ብር በላይ በሙስናና ብልሹ አሰራር ምክንያት ለምዝበራ እንደተጋለጠ ሲጠቅስ አሶሴሽን ኦፍ ሰርቲፋይድ ፍራውድ ኤግዛማይነር በምህፃረ ቃል ACFE በመባል የሚታወቀው ተቋም በበኩሉ ተቋማት በማጭበርበርና ሙስና አምስት በመቶ አመታዊ በጀታቸውን እንደሚያጡ ይጠቅሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እነዚህንና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ የማጭበርበር ኦዲት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ሲሆን ስልጠናውን ለተሳታፊዎች የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ እንዳሉት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ከመንግስት የሚፈቀድላቸውን ውስን በጀት ለተፈቀደላቸውና ለታለመለት አላማ በማዋል ተቋማት እራሳቸውን ከማጭበርበርና ምዝበራ የፀዱ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ዋና ኦዲተሩ አክለው በየተቋማቱ ጠንካራ የውስጥ ኦዲተሮች መኖራቸውን ጠቅሰው እነዚህ የተቋማት የውስጥ ኦዲተሮች ተቋማቱ የሚበጀትላቸውን ሀብት ከብክነት ለመታደግ ከፍተኛ ሚና ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው እነዚህ የተቋማት የውስጥ ኦዲት ሰራኞች ሚናቸውን በልኩ መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

********************************

የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም