አለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ!
አለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ!
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት «ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!» በሚል መሪ ቃል በዓለም ለ22ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ21 ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ ባስተላለፉት መልክት ተቋማችን ከሁሉም በላይ በሙስና ጉዳይ ተልእኮ ወስደን በተደራጀና ተቋማዊ አሰራር በሆነ ሁኔታ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን መከላከል እንደ ሀገር ደግሞ አዋጆች ደንቦች ወጥተዋል ይህን መሰረት አድርገን እንደ አንድ የኦዲት ባለሙያ ሙስናን መከላከል ብቻ ሳይሆን በሙስናና ብልሹ አሰራር የባከነን የመንግስትና የህዝብ ሀብት ማስመለስ ይገባል ብለዋል።
ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ አክለው በመስሪያ ቤቱ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመታገል አደረጃጀትና አንድ የስራ ክፍል ፈጥሮ በተግባር በፀረ ሙስናና ብልሹ ከሰራር ትግል ውስጥ መሆኑን በመግለፅ ሁሉም ሰራተኞች ለዛሬ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ከሙስናንና ብልሹ አሰራር የፃዳች ሀገር ለማስረከብ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ረቂቅ ምርምር እና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ ሙስና ማለት በግል ወይም በቡድን፣ በፖለቲካ መሪዎች ወይም በቢሮክራቶች ስልጣንና ሀላፊነትን መከታ በማድረግ የህዝብን ጥቅምና ፍላጎት ለግል ጥቅም የማዋል ኢ-ስነምግባርዊ ድርጊት ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ይህንና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ አለም አቀፍና አህጉራዊ የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽኖችን የተቀበለችና በርካታ እርምጃዎች እየወሰደች ትገኛለች እንደምትገኝ ጠቅሰው የስልጠናው ተሳታፊዎች የሙስና ወንጀልን ከመፈጸም በመቆጠብ ሌሎች እንዳይፈጽሙ ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ህዳር 18/2018 ዓ.ም
የኮምንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት



Leave a Reply