በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለሠራተኞች የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ
በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለሠራተኞች የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ
***********************************
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ እንደገለፁት መልካም ስነ ምግባርና ሙስናን መዋጋት ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ሳይሆን የእያንዳንዱ ሰራተኛ ድርሻና ተሳትፎ መሆኑን በመጥቀስ ሰራተኛው ስራውን በቅንነትና በታማኝነት በመስራት ለሌሎች አርአያ መሆን ይገባል ብለዋል፡፡
አክለውም የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የከተማዋን ሀብትና ንብረት በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን የሚያረጋግጥ ተቋም እንደመሆኑ መጠን የማጭበርበር ወይም የልዩ ኦዲትን በዳይሬክቶሬት ደረጃ በአዲስ መልክ በማደራጀት ሙስናንና ማጭበርበርን በመፋለም በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀስ እንደመሆኑ ፣ የሠራተኞቹ የሥነ-ምግባር ደረጃ ከማንኛውም ተቋም በላይ አርአያነት ያለው ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
የመንግስት ልማት ድርጅት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳሬክቶሬት አቶ ንጉስ ሽመልስ በበኩላቸው ሙስናን መከላከል የሚቻለው በጠንካራ የሕግ ተፈጻሚነት ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ ሠራተኛ የሥነ-ምግባር ባለቤት ሲሆንና የሙስናን አፀያፊነት በልኩ ሲረዳ መሆኑን ጠቅሰው ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በሥራ ላይ የሚያጋጥሙ የሥነ-ምግባር ብዥታዎችን ለመቅረፍና ሙያዊ ግዴታን በብቃት ለመወጣት የተሻለ ግንዛቤ መፍጠርን ያለመ ነው ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በቀጣይም የሙስና መከላከል ስትራቴጂውን በማጠናከር፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሠራር ለመገንባት እንደሚሠራ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ገልፀዋል።
*********************************
ሚያዝያ 9/2018 ዓ.ም
የኮሙንኬሽን ዳይሬክቶሬት


Leave a Reply