ኦዲተሮች የሚባክነውን ውስን የመንግስት እና የህዝብ ሀብት ከብክነትና ብልሹ አሰራር ለመታደግ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡
ኦዲተሮች የሚባክነውን ውስን የመንግስት እና የህዝብ ሀብት ከብክነትና ብልሹ አሰራር ለመታደግ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡
በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሚስተዋሉ የማጭበርበር Fraud ድርጊቶችን ተከትሎ የልዩ ኦዲት አስፈላጊነት እና ሚና በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት እየሳበ ይገኛል መንግስታዊና የግል ተቋማት ሙስስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን ተቋማት መፍትሄ የሚሏቸውን አማራጮች ሲወስዱ ይስተዋላል ይሁን እንጂ በሚፈለገው ልክ ውጤት አምጥቷል ለማለት አያስደፍርም።
በመሆኑም የማጭበርበር ተግባራት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማስቀረት በእውቀትና በክህሎት የሚመራ ኦዲተር ማፍራት ወሳኝ ሚና ያለው በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከከተማ አስተዳደሩ ለተውጣጡ የተመረጡ የውስጥ ኦዲተሮች ስለ ማጭበርበር/ ፍራውድ ተግባራት በሶስት ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
የአዲ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕ እንዳሉት ተቋማት በአሰራራቸው ቀልጣፋና ፍትሀዊ አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ በሙስናና ብልሹ አሰራር ምክንያት ተገልጋዩንና ህብረተሰቡን በአግባቡ ማገልገል ካልቻሉ ህብረተሰቡ በተቋሙ ብሎም በመንግስት አመኔታ ሊያጣ ይችላል ይህ እንዳይሆን ግን የሚሰሩ የሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ቀድሞ የመቆጣጠርና ተፈፅሞ ሲገኝም ተገቢ ማስተከካከያ እንዲሰጥ ለማድረግ የኦዲተሩ ሚና የላቀ ነው ብለዋል።
ዋና ኦዲተሩ አክለው ሙስናና ብልሹ አሰራር የሀገር ኢኮኖሚን በእጅጉ የሚጎዳ መሆኑን ጠቅሰው በተቋማት ውስጥ ያሉ ሁሉም የውስጥ ኦዲተሮች በያገባኛል ስሜት የሚባክነውን ውስን የመንግስት እና የህዝብ ሀብትን ከብክነትና ብልሹ አሰራር ለመታደግ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡



Leave a Reply