ክዋኔ ኦዲት ዋና አላማ ለመልካም አስተዳደር፣ ለተጠያቂነት እና ለግልፀኝነት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግን ያለመ ነው።
ክዋኔ ኦዲት ዋና አላማ ለመልካም አስተዳደር፣ ለተጠያቂነት እና ለግልፀኝነት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግን ያለመ ነው።
***********************************************
በአሁኑ ወቅት የተቋማትን ስራ ውጤታማነት ለማረጋገጥና አላስፈላጊ ብክነትን ለመቀነስ የክዋኔ ኦዲት (Performance Audit) ወሳኝ መሆኑ የታመነ ነው። የክዋኔ ኦዲት ተቋማት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በምን ያህል ደረጃ እየተወጡ እንደሆነ የሚመዘንበት አይነተኛ መሳሪያ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩን ተቋማት አፈፃፀም የተሻለ ለማድርግ በሶስት ዙር ለተመረጡ ከከተማ አስተዳደሩ ለተውጣጡ የውስጥ ኦዲተሮች የክዋኔ ኦዲት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
ለሁለተኛ ዙር የክዋኔ ኦዲት ስልጠና የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት ማናጀር የሆኑት አቶ መስፍን ውቤ እንዳሉት የአፈጻጸም/ክዋኔ ኦዲት አንድ ተቋም ግቡን ለማሳካት ሀብቱን እንዴት በብቃት እንደሚጠቀም የሚመረምር ገለልተኛ፣ ተጨባጭ እና አስተማማኝ ግምገማ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ቅልጥፍናና ውጤታማነትን በመገምገም፣ መሻሻል ያለባቸውን ቦታዎች በመለየት ለተቋማት የላቀ አፈፃፀም ምክረ ሃሳብ በማቅረብ በትኩረት የሚሰራ ነው ብለዋል።
አቶ መስፍን አክለው የክዋኔ ኦዲት በዋናነት በሶስት የ”E” መርሆዎች፤ Economy/ቁጠባ Efficiency/ብቃት Effectiveness/ውጤታማነትን አጣምሮ የያዘ መሆኑን ጠቅሰው የክዋኔ ኦዲት በመንግስት ሴክተር ተቋማት ውስጥ ለተሻሻለ ኢኮኖሚ፣ ቅልጥፍና እና ውጤታማነት አስተዋፅኦ በማድረግ፤ ለመልካም አስተዳደር፣ ለተጠያቂነት እና ለግልጽኝነት አሰራር የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግን ዓላማ ያደረገ የኦዲት ዘርፍ ነው ብለዋል፡፡
*****************************************
መጋቢት 3/2018 ዓ.ም


Leave a Reply